About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Saturday, December 20, 2014

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

ቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ በማዉጣት የምርጫ እንቅስቃሴዉም በዚያዉ አግባብ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በመጪዉ እሁድ በመላ አገርቱ በየምርጫ ጣቢያዉ መራጩ ህዝብና የፓርቲ ወኪሎችም በተገኙበት የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ይካሄዳል፡፡በገለልተኝነት የምርጫዉን ሂደት የህዝብ ዓይንና ጆሮ በመሆን የሚታዘቡ፣የምርጫዉን ፍተሃዊነትና ዴሞክራሲያዊነት የሚያረጋግጡ ናቸዉ፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸዉን እስከ ኅዳር 30 ድረስ ባለዉ ጊዜ ዉስጥ መርጠዋል፡፡

ቦርዱም በዛሬዉ ዕለት በካሄደዉ 004/2007 መደበኛ ስብሰባ ፓርቲዎቹ የመረጡዋቸዉን ምልክቶች ከተሻሻለዉ የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አኳያ መርምሮ ዕዉቅና ሰጥቷል፡፡
ይሁን እንጂ በሂደቱ ቦርዱን ያጋጠሙት ቀላልና ጥቂት ችግሮች ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ የተመረጡት ምልክቶች አልፎ አልፎ መመሳሰል፣ለህትመት ስራ አመች ያለመሆንና ግልጽነት የሚጎድላቸዉ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተገቢዉን ማስተካከያ እንዲያደርጉ ቦርዱ አስፈላጊዉን አመራር ሰጥቷል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ጠንከር ያለዉ ችግር በሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ ነበር፡፡ እነኚህ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸዉን ለጊዜዉ በሆደ ሰፊነት እንዲያስገቡ የተደረገ ቢሆንም በየፓርቲዎቹ የዉስጥ ጉዳይ ምክንያት በአመራሮች መካከል መከፋፈል በመፈጠሩ የፓርቲዎቹ ህጋዊና ትክክለኛ አመራሮች ያለመታወቅ ችግር ነበር፡፡

በመኢአድ ዉስጥ በተፈጠረ የዉስጥ ዲሞክራሲ እጦት ምክንያት 2003. ጀምሮ የምርጫ አዋጁንና የፓርቲዉን መተዳደሪያ ደንብ ባከበረ መልኩ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዶ ለቦርዱ ሪፖርት በማድረግ ማጸደቅ ያለመቻል፤ በየጊዜዉ «ደንብ አሻሽለናል፣አመራር ቀይረናል፣አዲስ ተመርጠናል» የሚሉ አካላት መፈጠሩ ትልቅ ችግር ነበር፡፡

በዚህ መሰረት ሐምሌ 14 ቀን 2005. ቦርዱ በማያዉቀዉና ቀርቦለት ዕዉቅና ባልተሰጠዉ መተዳደሪያ ደንብ አዲስ አመራሮች ተመርጠዋል፤
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ እስከ መስከረም ወር 2007. ድረስ እነዚህ አመራሮች በቦርዱ ዕዉቅና ባያገኙም የተጓደሉትን ጉዳዮች እናሟላለን በሚል ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡

የፓርቲዉን ዉስጠ ደንብና የምርቻ አዋጁን በጣሰ መልኩ ቀደም ሲል ከኃላፊነት ተነስተዋል የተባሉት ግለሰብ ቦርዱ በማያዉቀዉ ምክንያት ህጋዊ ያልሆነ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት የፓርቲዉን እንቅስቀሴ በዲጋሚ ተረክበናል ብለዉ ቀርበዋል፡፡

ይሄዉ ኃይል የጠቅላላ ጉባኤዉ ዉጤት ለቦርዱ እስከአሁን ባልቀረበበት ሁኔታ የፓርቲዉን አመራር/ፕረዝዴንት/ ነን በማለት እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ምርጫዉም የተካሄደዉ በደብዳቤ ለቦርዱ ከተገለጸለት ሰዓት ዉጭና ቦርዱ ተወካዮች ባልተገኙበት ነበር፡፡

ስለዚህ የመኢአድ ፕሬዝዴንት ማነዉ?/አቶ አበባዉ መሐሪ ወይስ / ኃይሉ ሻወል ወይስ አቶ ማሙሸት አማረ ? የሚለዉ እንቆቅልሽ ሆኖብናል፡፡

የትኛዉም ወገን ቢሆን የፓርቲዉን ዉስጠ ደንብና የምርጫ ህጉን በተከተለ መልኩ አመራር ስለመሆኑ ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ 

አንድነት ፓርቲን በተመለከተ ቦርዱ በማያዉቀዉና እዉቅና ባልሰጠዉ የመተዳደሪያ ደንብ፣አሻሻልኩ የሚለዉን ደንብም 7 ወራት ለቦርዱ ሪፖርት ሳያደርግ ሚስጥር አድርጎ አስቀምጠዋል፡፡ እንደገና ይሄንኑ ደንብ በመጠቀም / ግዛቸዉ ሽፈራዉን/የፓርቲዉን ፕሬዝደንት/ ከስልጣን አሰናብተዋል፡፡ በመቀጠልም ሌላ ፕሬዝደንት በምትካቸዉ በፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብም ሆነ በምርጫ አዋጁ በጠቅላላ ጉባኤ መመረጥ ያለበትን ወደ ጎን በመተዉ በብሔራዊ ምክር ቤት እንዲመረጥ አድርገዋል፡፡

ጠቅላላ ጉባኤዉም የተካሄደዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ በጣሰ መልኩ ምልዓተ ጉባኤ ባልተሟላበት፣ለጠቅላላ ጉባኤዉ በህጉ የተሰጡትን ስልጣኖች በብሔራዊ ምክር ቤቱ እንደወሰን በማድረግ ነበር፡፡

ይሄንን ተከትሎ የቀድሞዉ አመራር አላስፈላጊ ጫና ተፈጥሮባቸዉ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገዉ ከህግ ዉጭ በመሆኑ አሁን ተመረጥን ለሚሉት ቦርዱ ዕዉቅና እንዳይሰጥ የሚሉ በርካታ የፓርቲዉ አመራሮችና አባላት ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል የምርጫ ሂደቱ ያለብትን ግድፈት እናስተካክላለን በሚል አዲስ ተመርጠናል በሚሉት አካላት እንቅስቀሴ ቢደረግም ተስተካክሎ ለቦርዱ የቀረበ ነገር ባለመኖሩ ህጋዊ አመራሩን የመለየት ስራ ቦርዱ ማከናወን አልቻለም፡፡

ማጠቃለያ

መኢአድ

1.በፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብ በስራ ላይ ያለዉ 2001 በቦርዱ ዕዉቅና የተሰጠዉ ሲሆን አንቀጽ 20/1/ መሰረት ፕሬዝደንትና ምክትል ፕሩዝደንት የሚመረጠዉ በጠቅላላ ጉባኤዉ ከማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት መካከል ነዉ ይላል፡፡አሁን የተመረጡት ግን ከአባልነት ተሰርዘዉ 4 ዓመታት በላይ የቆዩ ወደ ጉባዔዉም የገቡት በአባልነት እንዲሳተፉ እንጂ እንዲመረጡ ደንባቸዉ አይደግፍም፡፡

2.መተዳደሪያ ደንቦችን ማሻሻል የፈለገ የፖለቲካ ፓርቲ አስቀድሞ ለቦርዱ ማሳወቅ እንዳለበት በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ 573/2000 አንቀጽ 12/2/ ፓርቲዉ ይሄንን ሳይፈጽም ደንቦች ያሻሸላል በቦርዱ ባልጸደቀ ደንብም እርምጃዎችን ይወስዳል፡፡ይህም ከአሰራር ዉጪ ነዉ፡፡

3. በፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ አንቀጽ 19/1() መሰረት የቦርድ ተወካይ ባልተገኘበት የጠቅላላ ጉባኤ መካሄዱና የአመራሮች ምርጫ ተደርጓል ይህ ህግም አሰራርም አይደለም፡፡

4. በፓርቲዉ መተደዳሪያ ደንብ አንቀጽ 10(2)(17) መሰረት በድጋሚ ካልተመረጠ በስተቀር የአመራር አባላትም ሆነ ሌሎች የማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት የስራ ዘመን አምስት ዓመት እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ይሄንን በተጻረረ መልኩ 2005 የተመረጠዉ አመራር አሉ የተባሉትን ጉድለቶች ለማስተካከል እንቅስቀሴ ላይ እያለ ሌላ አመራር በላዩ ላይ እንዲመረጥ ተደርጓል፡፡

5.የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሟላ ሰነድና ማህተም በተደገፈ ሪፖርት ለቦርዱ ማቅረብ እንደሚገባ በምዝገባ አዋጁ አንቀጽ 19 ስር የተደነገገ ቢሆንም ተካሄደ የተባለዉን ጠቅላላ ጉባኤ በተሟላ ሰነድ በማስደገፍ ማቅረብ አልቻለም፡፡

አንድነት

በስራ ላይ ያለዉ 2004. የመተዳደሪያ ድንብ

1.አንድነት ፓርቲ በተመለከተ ወቅታዊ የፓርቲዉ ጠቅላላ ሪፖርት በወቅቱ ያለማቅረብ ሰባት ወራት በማዘግየት አቅርባል፤ ይሄ ደግሞ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ .573/2000 አንቀጽ 19 እስከ 27 እንደዚሁም አንቀጽ 39 የጣሰ ከመሆኑም በላይ የፓርቲዉን የዉስጠ ደንብ ጥሱዋል፡፡

2. የፓርቲዉ አመራሮች ፕሬዝደንቱን ጨምሮ በጠቅላላ ጉባዔ እንደሚመረጥ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ .573/2000 አንቀጽ 8/2()/ስር ተመልክቷል፡፡ የፓርቲዉ ዉስጠ ድንብ አንቀጽ 13/1/ ስር «በጠቅላላ ጉባኤዉ ይመረጣል» የሚለዉን የጣሰና ፕሩዝደንቱ በጠቅላላ ጉባኤ መምረጥ ሲገባቸዉ በብሔራዊ ምክር ቤት ተመርጠዋል፡፡

3.የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ብዛት በተመለከተ በምዝገባ አዋጁ አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀጽ 1// የፓርቲዉን ስበሰባ እና ዉሳኔ አሰጣጥ ስነ ስርዓት ሊኖርዉ እንደሚገባ ይደነግጋል፡፡ የፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10/2/() የጠቅላላ ጉባኤ የድምጽና ዉሳኔ አሰጣጥ በአብላጫ ድምጸ/50 +1/ ይሆናል እያለ ይሄንን ባላከበረ መልኩ ፓርቲዉ ጠቅላላ ጉባዔዉን አካሂዷል፡፡

4. ፓርቲዉ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 11/1()/ መሰረት የፓርቲዉ መሪ እንዲሁም ስራ አስፈጻሚ ከህግ ወይም ከፓርቲዉ ፕሮግራም ዉጭ እየተንቀሳቀሰ ነዉ ብሎ ሲያምን 2/3 ድምጽ መሪዉን ጨምሮ ስራ አስፈጻሚዉን በማገድ የጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራና 6 ወራት ጊዜ ዉስጥ አዲስ ምርጫ እንዲደረግ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ስልጣን የተሰጠዉ እንጂ ፕሬዝደንት እንዲመርጥ ስልጣን ሳይኖረዉ ፈጽሟል፡፡

በመሆኑም እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ስለመረጡት ምልክት ቦርዱ የመጨረሻ ዉሳኔ ለመስጠት በመቸገሩ ጉዳያቸዉን አስተካክለዉ እንዲያቀርቡ ቦርዱ በዛሬዉ ዕለት 4/2007 መደበኛ ስብሰባዉ የአንድ ሳምንት ጊዜ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም የተደረገዉ ቦርዱ ከዚህ በፊትም በሆደ ሰፊነት ያለባቸዉን ችግሮቻቸዉን እነዲፈቱ ዕድል ሲሰጣቸዉ እንደነበር ሁሉ አሁንም በተሰጣቸዉ ጊዜ ዉስጥ የዉስጥ ጉዳያቸዉን በህጉ መሰረት በመፍታት እንዲያቀርቡ ለማስቻል ነዉ፡፡ ይሄ ካልተፈጸመ ቦርዱ ለሁለቱም ፓርቲዎቹ የሰጡትን ምልክት እዉቅና ለመስጠትና ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚቸገር አጥብቆ ያሳስባል፡፡ 

ታህሳስ 10/2007 .