About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Thursday, October 30, 2014

ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በፕረስ ኮንፈረንሱ ከተናገሩት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገራችን ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ይፋዊ ጥሪ በማድረግ እስካሁን በቦርዱ የተከናወኑ ስራዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ከተናገሩት ውስጥ
1.  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች 90 ፐርሰንት ያህሉን መጠናቀቃቸው፣
2.  ቦርዱ ያስፈፀማቸው አራት ጠቅላላ ምርጫዎች በመገምገም በሰው ኃይል ግንባታም ሆነ በሎጂስቲክስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አደረጃጀቱን ያጠናከረ መሆኑን እና በአስተማማኝ ደረጃ መድረሱ፣
3.  በጊዜ ሰሌዳው ላይ ቀደም ሲል የፖለቲካ ፓርዎች ከቦርዱ ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች ማለትም
Ø  ጥቅምት 7/2007 ዓ.ም ጥሪ ከተደረገላቸው 23 አገር ዓቀፍ ፓርቲዎች  22 በመገኘት
Ø  ጥቅምት 8/ 2007 ዓ.ም በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል የሚገኙ 19 ክልላዊ ፓርቲዎች በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ውጪ የሚገኙ 26 ክልላዊ ፓርቲዎች በአዳማ  ከተማ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ በጊዜ ሰሌዳው ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ እንዲሁም በተሰጠው የ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ አስተያየት በፅሑፍ እንዲያቀርቡ ዕድል ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች በተዘጋጀው መድረክ ገንቢ አስተያየታቸው ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ አስተያየታቸውን በፅሑፍ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በመነሳትም ቦርዱ ፓርቲዎች የሰጡትን አስተያየት በጥልቀት በመመርመር ገንቢ አስተያየቶችን በማካተት የጊዜ ሰሌዳውን አፅድቋል፡፡

No comments: