About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Friday, October 31, 2014

DATA OF THE 2010 GENERAL ELECTION

TOTAL DATA OF THE 2010 GENERAL ELECTION
Number of Competing Political Parties and Private candidates in the 2010 General Election.

                       No
Competing Candidates
House of Peoples’ Representative            
Regional Council
Number of Political parties
Female
Male
Total
Female
Male
Total
1
Political Party
272
1,916
2,188
725
4,021
4,746

63
2
Private
1
33
34
2
9
11
Total
273
1,949
2,222
727
4,030
4,757
                      Total candidates who competed for both councils.
v  Female = 1,000 (14.3%)
v  Male = 5,979 (85.7 %)
v  Total = 6,979

Participation of the public in the 2010 General Election.          
                                                                                                
No
Participation
Public Participation in Number        
Public Participation in Percentile
Female
Male
Total
Female
Male
Total
1
Registered
15,252,240
16,674,280
31,926,520
47.8
52.2
100
2
Ballot Casters
14,214,737
15,617,453
29,832,190
93.19
93.66
93.4
3
Non-Casters
1,037,503
1,056,827
2,094,330
6.8
6.34
6.6


A summary of final results of the 2010 General Election
To the House of Peoples’ Representatives (HPR)

No.
Winner Party
Results Obtained
1
The Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF)
    499
2
The Somali People’s Democratic Party (SPDP)
       24
3
The Benishangul Gumuz Peoples Democratic Party (BGPDP)
         9
4
The Afar National Democratic Party (ANDP)
         8
5
The Gambela People’s Unity Democratic Movement (GPUDM)
         3
6
The Harari National League (HNL)
         1
7
The Argoba People Democratic Organization (APDO)
         1
8
The Ethiopian Federal Democratic Unity Forum (Medrek)
         1
9
Independent
         1
Total number of seats in the House of Peoples’ Representatives
     547

  To Regional State Councils (RSC)

No.
Regional State
No. seats
Winner Party
Results Obtained
1
Tigray
152
The Tigray People’s Liberation Front (TPLF-EPRDF)
152
2
Afar
96
The Afar National Democratic Party (ANDP)
93
The Argoba People’s Democratic Organization (APDO)
3
3
Amhara
294
The Amhara National Democratic Movement (ANDM-EPRDF)
294
4
Oromia
537
The Oromo People’s Democratic Organization (OPDO/EPRDF)
537
5
Somali
186
The Somali People’s Democratic Party (SPDP)
186
6
Benishangul Gumuz
99
The Benishangul Gumuz Peoples Democratic Party (BGPDP)
98

The All Ethiopian Unity Organization (AEUO)
1
7
SNNP
348
The Southern Ethiopian People’s Democratic Movement (SEPDM-EPRDF )
348
8
Gambella
156
The Gambela People’s Unity Democratic Movement (GPUDM)
156
9
Harari
36
The Oromo People’s Democratic Organization (OPDO/EPRDF)
18
The Harari National League (HNL)
18
Total number of seats in the 9 Regional States
1,904



Thursday, October 30, 2014

ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በፕረስ ኮንፈረንሱ ከተናገሩት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገራችን ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ይፋዊ ጥሪ በማድረግ እስካሁን በቦርዱ የተከናወኑ ስራዎች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በሚኒስትር ማዕረግ የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ከተናገሩት ውስጥ
1.  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው ምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች 90 ፐርሰንት ያህሉን መጠናቀቃቸው፣
2.  ቦርዱ ያስፈፀማቸው አራት ጠቅላላ ምርጫዎች በመገምገም በሰው ኃይል ግንባታም ሆነ በሎጂስቲክስ ከመቼውም ጊዜ በላይ አደረጃጀቱን ያጠናከረ መሆኑን እና በአስተማማኝ ደረጃ መድረሱ፣
3.  በጊዜ ሰሌዳው ላይ ቀደም ሲል የፖለቲካ ፓርዎች ከቦርዱ ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች ማለትም
Ø  ጥቅምት 7/2007 ዓ.ም ጥሪ ከተደረገላቸው 23 አገር ዓቀፍ ፓርቲዎች  22 በመገኘት
Ø  ጥቅምት 8/ 2007 ዓ.ም በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል የሚገኙ 19 ክልላዊ ፓርቲዎች በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ውጪ የሚገኙ 26 ክልላዊ ፓርቲዎች በአዳማ  ከተማ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ በጊዜ ሰሌዳው ላይ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ እንዲሁም በተሰጠው የ 15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ አስተያየት በፅሑፍ እንዲያቀርቡ ዕድል ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት አብዛኛዎቹ ፓርቲዎች በተዘጋጀው መድረክ ገንቢ አስተያየታቸው ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ አስተያየታቸውን በፅሑፍ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በመነሳትም ቦርዱ ፓርቲዎች የሰጡትን አስተያየት በጥልቀት በመመርመር ገንቢ አስተያየቶችን በማካተት የጊዜ ሰሌዳውን አፅድቋል፡፡

ምርጫ ቦርድ የመጪውን 5ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ፡፡




የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የ2007 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ

ተ.ቁ
ክንውን
ቀን
1
በምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገኝተው የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት፤
ከሕዳር 15 እስከ ሕዳር 30 ቀን 2007 ዓ.ም
2
የምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች ተከፍተው ሥራቸውን በይፋ የሚጀምሩበት፤
ታህሳስ 1 ቀን 2007 ዓ.ም
3
መራጩ ሕዝብ በየምርጫ ጣቢያው በይፋ በሚደረግለት ጥሪ መሠረት በሚያካሂደው የአንድ ቀን ስብሰባ የምርጫ ጣቢያ የሕዝብ ታዛቢዎችን የሚመረጥበት፤
ታህሳስ 12 ቀን 2007 ዓ.ም
4
በግል ዕጩነት ለመወዳደር የሚፈልጉ ከቦርዱ ዋና ጽ/ቤት ወይም ከክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቅፅ ናሙና የሚያገኙበት እና መወዳደር በፈለጉበት የምርጫ  ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች እየተዘዋወሩ የድጋፍ ፊርማቸውን የሚያሰባስቡበት እና በቀበሌ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት እንዲጣራ የሚያስረክቡበት፤
ከታህሳስ 6 እስከ ታሕሳስ 25 ቀን 2007 ዓ.ም
5
የቀበሌ መስተዳድሮች የተሰባሰበውን የድጋፍ ፊርማ ትክክለኛነት እያጣሩ በቀበሌው ማህተም አረጋግጠው ለድጋፍ ፊርማ አሰባሳቢዎች የሚያስረክቡበት፤
ከታህሳስ 10 እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም
6
የግል ተወዳዳሪዎች ያቀረቡትን የድጋፍ ፊርማ ትክክለኛነት በማጣራት ሂደት ሕጋዊ በሆነ ምክንያት ከተሰረዘባቸው በተጓደለባቸው የድጋፍ ፊርማ ምትክ አዲስ ፊርማ አሰባስበው ትክክለኛነቱን እንዲጣራላቸው ለቀበሌ መስተዳድር ጽሕፈት ቤቶች የሚያቀርቡበት እና የተጣራ የድጋፍ ፊርማ ለምርጫ ክልል ጽ /ቤቶች የሚያቀርቡበት፤
ከታህሳስ 15 እስከ ታህሳስ   30 ቀን 2007 ዓ.ም
7
በምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና በግል ለመወዳደር የድጋፍ ፊርማ ያሰባሰቡ ዕጩዎች በምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት እና በየምርጫ ጣቢያ ለይተው የመደቧቸውን ተቀማጭና ተዘዋዋሪ ወኪሎቻቸውን ለምርጫ ክልል ጽ/ቤት የሚያሳውቁበት፤
ከታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓ.ም እስከ ግንቦት 5 ቀን 2007 ዓ.ም
8
የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች ምዝገባ በየምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት የሚካሄድበት፤
ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 27 ቀን 2007 ዓ.ም
9
በግል ምርጫ ለመወዳደር ድጋፍ ያሰባሰቡ ግለሰቦች በቀበሌ መስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ትክክለኛነቱ ተጣርቶ የተሰጣቸውን የድጋፍ ፊርማ በተጠቋሚ ዕጩነት ለመመዝገብ ለምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት የሚያቀርቡበት፤
ከታህሳስ 16 ቀን  እስከ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም
10
በፓርቲም ሆነ በግል ለመወዳደር የቀረበ ማንኛውም ሰው በዕጩነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥም አቤቱታውን ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚያቀርብበትና ውሣኔ የሚያገኝበት፤
ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም
11
በፓርቲም ሆነ በግል ለመወዳደር ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ለምርጫ ክልል ጽ/ቤት አቅርቦ በተሰጠው ውሣኔ ቅሬታ ካለው ይግባኝ ለክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቅርቦ ውሣኔ የሚያገኝበት፤
ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 30 ቀን 2007 ዓ.ም
12
የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው ሥራቸውን በይፋ የሚጀምሩበት፤
ታህሳስ 30  ቀን 2007 ዓ.ም
13
የመራጮች  ምዝገባ   በየምርጫ  ጣቢያው የሚካሄድበት፤
ከጥር 1 ቀን እስከ የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም
14
ማንኛውም ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ያጋጠመው መራጭ ለመራጮች ምዝገባ በተወሰኑት ቀናት ሊመዘገብ ያልቻለ ለመሆኑ ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አቅራቢ ሲወሰን በመራጭነት የሚመዘገቡበት ልዩ የምዝገባ ቀን፤
የካቲት 13 እና የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም
15
የመራጮች መዝገብ በየምርጫ ጣቢያው ለሕዝብ ይፋ ሆኖ የሚቆይበት፤
ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 19 ቀን 2007 ዓ.ም
16
በመራጭነት ከመመዝገብ የታገደ ወይም ያለአግባብ ተመዝግቧል ተብሎ ለቀረበ አቤቱታ የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚያቀርቡበት፤
ከጥር 1 ቀን እስከ የካቲት  23 ቀን 2007 ዓ.ም
17
የዕጩዎችን ማጣሪያ አልፈው የተመዘገቡ የግል ዕጩዎች የመወዳደሪያ ምልክታቸውን በምርጫ ክልል ጽ/ቤት ተገኝተው የሚመርጡበት፤
ከጥር 26 ቀን እስከ ጥር  30 ቀን 2007 ዓ.ም
18
የዕጩዎች ዝርዝር ለየምርጫ ክልሉ ሕዝብ ይፋ የሚደረግበት፤
የካቲት 1 ቀን 2007 ዓ.ም
19
የዕጩነት ማረጋገጫ መታወቂያ ካርድ የሚሰጥበት፤
ከየካቲት 2 ቀን እስከ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም
20
የዕጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ በይፋ የሚጀመርበት፤
የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም
21
ስለ ድምጽ አሰጣጡ ሂደት ለመራጮች የአንድ ቀን ገለጻ በየቀበሌው ሚሰጥበት፤
ግንቦት 9 ቀን 2007 ዓ.ም
22
የዕጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ በይፋ የሚጠናቀቅበት፤
ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት
23
የድምጽ መስጫ ዕለት፤
ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት
24
የድምጽ ቆጠራ ወዲያውኑ በየምርጫ ጣቢያው የሚከናወንበት፤
ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ
25
በድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ለምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚያቀርብበትና ውሳኔ የሚያገኝበት፤
ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም
26
የድምጽ ቆጠራ ሂደትና ውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው ቅሬታውን ለምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አስመዝግቦ አቤቱታውን በየደረጃው ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ እና ለቦርዱ የሚያቀርብበትና ውሣኔ የሚያገኝበት፤
ከግንቦት  16 ቀን እስከ ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም
27
የድምጽ ቆጠራ ውጤት ለየምርጫ ጣቢያው ለሕዝብ በማስታወቂያ ሰሌዳ በይፋ  የሚገለጽበት፤
ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ.ም
28
በየምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ ውጤት በሚገኙበት  የምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት የሚዳመርበትና ውጤቱ በማስታወቂያ ሰሌዳ ለሕዝብ በይፋ የሚገለፅበት፤
ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም
29
ቦርዱ በአጠቃላይ የምርጫ ውጤት ከየምርጫ ክልሉ ተጠናቆ እስኪደርሰው ድረስ እንደአስፈላጊነቱ ከየምርጫ ክልሉ የመጣለትን የምርጫ ውጤት በጊዜያዊነት በቦርዱ ጽሕፈት ቤት ይፋ የሚያደርግበት፤
እስከ ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም
30
የምርጫው አጠቃላይ ውጤት በብሔራዊ ደረጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚፀድቅበትና ውጤቱ በይፋ ለሕዝብ የሚገለፅበት::
ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ጥቅምት 2007 ዓ.ም.