የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የ2007 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ
ሰሌዳ
ተ.ቁ
|
ክንውን
|
ቀን
|
1
|
በምርጫ
የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገኝተው የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን የሚመርጡበት፤
|
ከሕዳር
15 እስከ ሕዳር 30 ቀን 2007 ዓ.ም
|
2
|
የምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች ተከፍተው ሥራቸውን በይፋ የሚጀምሩበት፤
|
ታህሳስ 1 ቀን 2007 ዓ.ም
|
3
|
መራጩ
ሕዝብ በየምርጫ ጣቢያው በይፋ በሚደረግለት ጥሪ መሠረት በሚያካሂደው የአንድ ቀን ስብሰባ የምርጫ ጣቢያ የሕዝብ ታዛቢዎችን የሚመረጥበት፤
|
ታህሳስ
12 ቀን 2007 ዓ.ም
|
4
|
በግል
ዕጩነት ለመወዳደር የሚፈልጉ ከቦርዱ ዋና ጽ/ቤት ወይም ከክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቅፅ ናሙና የሚያገኙበት
እና መወዳደር በፈለጉበት የምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች
እየተዘዋወሩ የድጋፍ ፊርማቸውን የሚያሰባስቡበት እና በቀበሌ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት እንዲጣራ የሚያስረክቡበት፤
|
ከታህሳስ
6 እስከ ታሕሳስ 25 ቀን 2007 ዓ.ም
|
5
|
የቀበሌ
መስተዳድሮች የተሰባሰበውን የድጋፍ ፊርማ ትክክለኛነት እያጣሩ በቀበሌው ማህተም አረጋግጠው ለድጋፍ ፊርማ አሰባሳቢዎች የሚያስረክቡበት፤
|
ከታህሳስ
10 እስከ ታህሳስ 27
ቀን 2007
ዓ.ም
|
6
|
የግል
ተወዳዳሪዎች ያቀረቡትን የድጋፍ ፊርማ ትክክለኛነት በማጣራት ሂደት ሕጋዊ በሆነ ምክንያት ከተሰረዘባቸው በተጓደለባቸው የድጋፍ
ፊርማ ምትክ አዲስ ፊርማ አሰባስበው ትክክለኛነቱን እንዲጣራላቸው ለቀበሌ መስተዳድር ጽሕፈት ቤቶች የሚያቀርቡበት እና የተጣራ
የድጋፍ ፊርማ ለምርጫ ክልል ጽ /ቤቶች የሚያቀርቡበት፤
|
ከታህሳስ
15 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም
|
7
|
በምርጫ
የሚወዳደሩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና በግል ለመወዳደር የድጋፍ ፊርማ ያሰባሰቡ ዕጩዎች በምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት እና በየምርጫ
ጣቢያ ለይተው የመደቧቸውን ተቀማጭና ተዘዋዋሪ ወኪሎቻቸውን ለምርጫ ክልል ጽ/ቤት የሚያሳውቁበት፤
|
ከታህሳስ
5 ቀን 2007 ዓ.ም እስከ ግንቦት 5 ቀን 2007 ዓ.ም
|
8
|
የፖለቲካ
ፓርቲ ዕጩዎች ምዝገባ በየምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤት የሚካሄድበት፤
|
ከታህሳስ
16 እስከ ጥር 27 ቀን 2007 ዓ.ም
|
9
|
በግል
ምርጫ ለመወዳደር ድጋፍ ያሰባሰቡ ግለሰቦች በቀበሌ መስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ትክክለኛነቱ ተጣርቶ የተሰጣቸውን የድጋፍ ፊርማ
በተጠቋሚ ዕጩነት ለመመዝገብ ለምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት የሚያቀርቡበት፤
|
ከታህሳስ
16 ቀን እስከ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም
|
10
|
በፓርቲም
ሆነ በግል ለመወዳደር የቀረበ ማንኛውም ሰው በዕጩነት ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ሲያጋጥም አቤቱታውን ለምርጫ ክልሉ አቤቱታ
ሰሚ ኮሚቴ የሚያቀርብበትና ውሣኔ የሚያገኝበት፤
|
ከታህሳስ
16 እስከ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም
|
11
|
በፓርቲም
ሆነ በግል ለመወዳደር ከመመዝገብ የሚያግድ ሁኔታ ያጋጠመው ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ለምርጫ ክልል ጽ/ቤት አቅርቦ በተሰጠው
ውሣኔ ቅሬታ ካለው ይግባኝ ለክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቅርቦ ውሣኔ የሚያገኝበት፤
|
ከታህሳስ
16 እስከ ጥር 30 ቀን 2007 ዓ.ም
|
12
|
የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው ሥራቸውን በይፋ የሚጀምሩበት፤
|
ታህሳስ
30 ቀን 2007 ዓ.ም
|
13
|
የመራጮች ምዝገባ በየምርጫ ጣቢያው
የሚካሄድበት፤
|
ከጥር 1 ቀን እስከ የካቲት
12
ቀን 2007
ዓ.ም
|
14
|
ማንኛውም
ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ያጋጠመው መራጭ ለመራጮች ምዝገባ በተወሰኑት ቀናት ሊመዘገብ ያልቻለ ለመሆኑ ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ
ሰሚ ኮሚቴ አቅራቢ ሲወሰን በመራጭነት የሚመዘገቡበት ልዩ የምዝገባ ቀን፤
|
የካቲት
13 እና የካቲት 14 ቀን 2007 ዓ.ም
|
15
|
የመራጮች መዝገብ በየምርጫ ጣቢያው ለሕዝብ ይፋ ሆኖ የሚቆይበት፤
|
ከየካቲት
15 እስከ የካቲት 19 ቀን 2007 ዓ.ም
|
16
|
በመራጭነት
ከመመዝገብ የታገደ ወይም ያለአግባብ ተመዝግቧል ተብሎ ለቀረበ አቤቱታ የምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም
ይግባኝ ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚያቀርቡበት፤
|
ከጥር
1 ቀን እስከ የካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም
|
17
|
የዕጩዎችን
ማጣሪያ አልፈው የተመዘገቡ የግል ዕጩዎች የመወዳደሪያ ምልክታቸውን በምርጫ ክልል ጽ/ቤት ተገኝተው የሚመርጡበት፤
|
ከጥር
26 ቀን እስከ ጥር 30 ቀን 2007 ዓ.ም
|
18
|
የዕጩዎች ዝርዝር ለየምርጫ ክልሉ ሕዝብ ይፋ የሚደረግበት፤
|
የካቲት
1 ቀን 2007 ዓ.ም
|
19
|
የዕጩነት ማረጋገጫ መታወቂያ ካርድ የሚሰጥበት፤
|
ከየካቲት
2 ቀን እስከ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም
|
20
|
የዕጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ በይፋ የሚጀመርበት፤
|
የካቲት
7 ቀን 2007 ዓ.ም
|
21
|
ስለ
ድምጽ አሰጣጡ ሂደት ለመራጮች የአንድ ቀን ገለጻ በየቀበሌው ሚሰጥበት፤
|
ግንቦት
9 ቀን 2007 ዓ.ም
|
22
|
የዕጩዎች የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ በይፋ የሚጠናቀቅበት፤
|
ግንቦት
13 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት
|
23
|
የድምጽ መስጫ ዕለት፤
|
ግንቦት
16 ቀን 2007 ዓ.ም ከጠዋቱ
12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት
|
24
|
የድምጽ ቆጠራ ወዲያውኑ በየምርጫ ጣቢያው የሚከናወንበት፤
|
ግንቦት
16 ቀን 2007 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ
|
25
|
በድምጽ
አሰጣጥ ሂደት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ለምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ የሚያቀርብበትና ውሳኔ የሚያገኝበት፤
|
ግንቦት
16 ቀን 2007 ዓ.ም
|
26
|
የድምጽ
ቆጠራ ሂደትና ውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ሰው ቅሬታውን ለምርጫ ጣቢያ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አስመዝግቦ አቤቱታውን በየደረጃው
ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ እና ለቦርዱ የሚያቀርብበትና ውሣኔ የሚያገኝበት፤
|
ከግንቦት 16 ቀን እስከ ሰኔ 7 ቀን 2007 ዓ.ም
|
27
|
የድምጽ
ቆጠራ ውጤት ለየምርጫ ጣቢያው ለሕዝብ በማስታወቂያ ሰሌዳ በይፋ
የሚገለጽበት፤
|
ግንቦት
17 ቀን 2007 ዓ.ም
|
28
|
በየምርጫ
ጣቢያዎች የድምጽ ቆጠራ ውጤት በሚገኙበት የምርጫ ክልል ጽሕፈት
ቤት የሚዳመርበትና ውጤቱ በማስታወቂያ ሰሌዳ ለሕዝብ በይፋ የሚገለፅበት፤
|
ግንቦት
22 ቀን 2007 ዓ.ም
|
29
|
ቦርዱ
በአጠቃላይ የምርጫ ውጤት ከየምርጫ ክልሉ ተጠናቆ እስኪደርሰው ድረስ እንደአስፈላጊነቱ ከየምርጫ ክልሉ የመጣለትን የምርጫ ውጤት
በጊዜያዊነት በቦርዱ ጽሕፈት ቤት ይፋ የሚያደርግበት፤
|
እስከ
ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም
|
30
|
የምርጫው
አጠቃላይ ውጤት በብሔራዊ ደረጃ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚፀድቅበትና ውጤቱ በይፋ ለሕዝብ የሚገለፅበት::
|
ሰኔ
15 ቀን 2007 ዓ.ም
|
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥቅምት 2007 ዓ.ም.
No comments:
Post a Comment