About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Thursday, October 23, 2014

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ2ዐዐ7 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ምክክር አደረገ፡፡


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ2ዐዐ7 ዓ.ም ለሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት ከሀገራዊና የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በረቂቅ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት አደረገ፡፡
በሚኒስትር ማዕረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በ07/02/2007 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ከሀገር ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በ08/02/2007 ዓ.ም በአዳማ ሪዞርት በተደገው የምክክር ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ቦርዱ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በልዩ ልዩ ዓበይት ወይም ቁልፍ ወቅታዊ ጉዳዮች እና በፓርቲዎቹ አጠቃላይ ሕጋዊ እንቅስቃሴ ላይ በተለያዩ ጊዜያት የጋራ ምክክር ሲያደርግ መቆየቱ አውስተው አሁንም ቦርዱ በ2007 ዓ.ም በሚያካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በመላው የሀገሪቱ ክልሎች ለማስፈፀም እና ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በምርጫው መላው የሀገራችን ሕዝቦች እና በሕጋዊ መንገድ በቦርዱ እውቅና አግኝተው እና ተመዝግበው ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከቦርዱ ጋር ተቀራርበውና ተባብረው ብዙ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ያሉት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ምርጫው ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በተሻለ መልኩ ያሳተፈ እና ፍሬያማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቦርዱ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ ጨምረውም በ2ዐዐ6 ዓ.ም በተደረጉ የቅድመ ምርጫ ምዕራፍ እንቅስቃሴ በርካታ ሥልጠናዎች ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ ለፍትሕ አካላት፣ ለሲቪክ ማህበራት እንደተሰጠ ገልፀው ቦርዱ አሁንም ተመሳሳይ ሥልጠና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ለመስጠትና አቅማቸውን ለማጎልበት ጠንክሮ ይሠራል ነው ያሉት፡፡ የዋና እና የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን በሰው ኃይል አስላለፍ የተሻለና ጠንካራ የምርጫ ተቋም ለማድረግ ብዙ ርቀት ሄዷል ያሉት ፕሮፌሰሩ የተሻለ የምርጫ አፈፃፀም እንዲኖር በርካታ አዳዲስ ሠራተኞች በችሎታና በብቃት ለመቅጠር በምልመላ ላይ እንገኛለን ብለው የነባሩን ሠራተኞች አቅም በመገንባት የተሻለ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት አቅማቸውን ገንብተናል ሲሉ ገለፀዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና በሃዋሳ ቲና ሆቴል ለደቡብ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች በተዘጋጀው የጋራ የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቦርዱ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔር በበኩላቸው በአጠቃላይ ቦርዱ የዘንድሮውን 5ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ በተሻለ ሁኔታ ለማካሄድና የተሳካ ለማድረግ ቀደም ሲል ካካሄዳቸው ጠቅላላ እና የአካባቢ ምርጫዎች በተገኙት ተሞክሮዎች እና ከሌሎች በርካታ የዓለም ሀገሮች የዲሞክራሲያዊ ምርጫ አስተዳደር ላይ የተገኙት ልምዶችን እንደሚጠቀም ጠቁመዋል፡፡

ከግራ ወደ ቀኝ ዶ/ር አዲሱ ገ/ሔር የቦርዱ ም/ሰብሳቢ፣ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና የቦርዱ ሰብሳቢ እና አቶ ነጋ ዱፊሳ የፅ/ቤቱ ዋና ኃላፊ

በቀጣዮቹ 8 ወራት ውስጥ ቦርዱ ሥራውን የበለጠ ለማቀላጠፍና በ2007 ዓ.ም በመላው ሀገሪቱ የሚካሄደው 5ኛ ዙር ጠቅላላ ምርጫ እንቅስቃሴን የሚቆጣጠርና ተግባራዊ የሚያደርግ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ እንደተዘጋጀ የገለፁት ዶ/ር አዲሱ የጊዜ ሰሌዳው 30 የተለያዩ ክንውኖች እንዳሉትም ገልፀዋል፡፡ ምርጫው በሀገር አቀፍ እና በክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች በሦስት የተለያዩ ቦታዎች በተደረገው የምክክር መድረክ ለእያንዳንድ የሥራ ክንውን የተቀመጡትን በጥሞና በመመርመር የተለመደውን ገንቢ ሃሳብ በመስጠት ሰነዱ እንዲዳብር መድረክ የተዘረጋ ሲሆን በዚህ መልኩ ይህ ስብሰባ የበለጠ ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም በመድረኩ አጠቃላይ አስተያየት እና ዝርዝር አስተያየት ደግሞ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ በጽሑፍ በመላክ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

አገር አቀፍ የፖለቲካ ድርጅቶች ከቦርዱ ጋር ምክክር ሲያደርጉ

በመጨረሻም የጊዜ ሰሌዳው ላይ የሚቀርቡ ገንቢ አስተያየቶች በማጠናቀር ለቦርድ አቅርበን እንደየአግባብነታቸው በመጠቀም በቅርብ ቀናት እናፀድቃለን ያሉት ዶ/ር አዲሱ ቦርዱ ያጸደቀዉንም ወዲያውኑ ለሕዝብ በሚዲያ እናደርሳለን ብለዋል፡፡
በእነዚህ የውይይት መድረኮች ላይ ሀገራዊና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጊዜ ሰሌዳው አጠቃላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ዝርዝር ሃሳባቸውን በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ለቦርዱ እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል፡፡

3 comments:

Anonymous said...

This time is the election time. The people of Ethiopia wants to see the process of the election in a credible and transparent manner. Show and inform the citizen on what's going on at the ground.

ETHIOPIAN ELECTION የኢትዮጵያውያን ምርጫ said...

Thanks for the comment, i will try to inform you what's going on at the institution.Your comment is highly appreciated.

Anonymous said...

soooo cooolllll