About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Tuesday, December 13, 2011

ስለ ማሟያ ምርጫ ምንነት


ምርጫ የአንድ ሀገር ህዝብ የሉዓላዊነት መገለጫ ነው፡፡ ህዝቦች በነፃነትና በቀጥታ በመሳተፍ ያስተዳድሩኛል ብለው ያመኑባቸውን ወኪሎቻቸውን የሚመርጡትና ፈቃዳቸውን የሚገልፁት በምርጫ ብቻ ነው፡፡ በሀገራችን ምርጫ የማስፈፀም ሥልጣንና ኃላፊነት በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 102 መሰረት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም በተሻሻለው የምርጫ ህግ 532/1999 ዓ.ም. መሠረት አምስት የምርጫ ዓይነቶች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን እነሱም፡- የጠቅላላ፣ የአካባቢ፣ የማሟያ፣ የድጋ የህዝ ውሳኔ ምርጫዎች ናቸው፡፡
ከእነዚህ የምርጫ አይነቶች አንዱ የማሟያ ምርጫ ሲሆን የማሟያ ምርጫ በይውረድልን ወይም በማንኛውም ምክንያት በየደረጃው የሚገኙ የተጓደሉ የምክር ቤት አባላት መቀመጫዎችን ለማሟላት የሚካሄድ የምርጫ ዓይነት ነው፡፡ በተሻሻለው የምርጫ ህግ ቁጥር 532/1999 .. አንቀጽ 30 መሠረት የማሟያ ምርጫ የሚካሄደው በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች በተለያዩ ምክንያት የተጓደሉባቸው አባላት እንዲሟላቸው ለቦርዱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በህጉ መሠረት የቀረበ የይውረድልን ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ቦርዱ ጥያቄው በደረሰው 3 ወር ጊዜ ውስጥ የማሟያ ምርጫ ያካሂዳል፡፡ ሆኖም አንድ ምክር ቤት የሥራ ዘመኑ ሊያልቅ 6 ወር የቀረው ከሆነ የማሟያ ምርጫው እንደማይካሄድ በዚሁ አንቀጽ ተደንግጓል፡፡
ማሟያ ምርጫ አፈፃፀም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተጣለበትን ህገ መንግሥታዊ ኃላፊነት ለመወጣት በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱ የተለያዩ ምርጫዎችን ገለልተኛ ሆኖ በብቃት እያስፈፀመ የመጣ አቅምና ልምድ ያካበተ ተቋም ነው፡፡ በ1994፣ በ1990 እና 2001 ዓ.ም በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ የተረጋጋ፣ ሰላማዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ የማሟያ ምርጫ አካሂዷል፡፡ በተመሳሳይ በዚህ በ2003 የበጀት ዓመት የህዝቡ የዕለት ተዕለት አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በቅርበት ለመፍታት የሚችሉ የምክር ቤት አባላት እንዲሟሉ የሚደረግበትን የማሟያ ምርጫበህጉ መሠረት ከኦሮሚያ ክልል፣ ከደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል እና ከአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤቶች የቀረበለትን ጥያቄ መርምሮ የምክር ቤቶቹ ቀሪ የሥራ ዘመን 6 ወር በላይ መሆኑን በማረጋገጥ የማሟያ ምርጫውን በነፃ፣ ፍትሃዊነትና በሰላማዊነት አካሂዷል፡፡ የማሟያ ምርጫ በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤት አባላት የህዝቡን ማህበራዊ፣ ኖሚ ፖለቲካዊ ችግሮች በቅርበት በሙሉ አቅማቸው መወሰንና ተግባራዊ ማድረግ እንዲችሉ እድል የሚሠጥ ነው፡፡ በተለይም የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች የህዝቡን አስተዳደራዊ ችግሮች በቀጥታና በቅርበት ተገኝተው የሚፈቱበት በመሆኑ ህዝቡ በዚህ የማሟያ ምርጫ ከምዝገባ እስከ ምርጫው ቀን ድረስ በን በመሳተፍ ወኪሎቹን መምረጥ ችሏል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለማሟያ ምርጫ የሚሰጡት ትኩረት አናሳ መሆኑ በሂደቱ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የማሟያ ምርጫ ደግሞ ወደፊትም ጥያቄ ሲቀርብ የሚካሄድና የቦርዱ መደበኛ ስራ ሆኖ የሚቀጥል ነው፡፡ በመሆኑም ቦርዱ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ችግሩን ለማሻሻልና ወደፊት በሚካሄዱ ምርጫዎች ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሕዝቡ ይበልጥ በንቃት ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የመራጮችና ሥነ ዜጋ ትምህርት ከወዲሁ ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቌል፡፡




No comments: