About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Tuesday, December 13, 2011

የምርጫ ቦርዱ እያከናወናቸው ያለ የአቅም ግንባታ ስራዎች!


በአለም አቀፍ ደረጃ ስለ አቅም ግንባታ የተለያዩ ባለሙያዎች በተለያዩ ወቅቶች  ትርጓሜ  የሰጡ ሲሆን  ከነዚ  መካከል ብዙዎቹ   ሚያመሳስላቸው ባህሪያት ዋናነት ተቋማትን ማጠናከር ፣ ማስተባበር፣ ተልዕኮን በታቀደ  መንገድ ማስፈፀም የሚሉ  ሲሆኑ  አቅምን በማጎልበት የአመራሩን እና ተቋማትን ውጤት በማሻሻል ለችግሮቹ መፍትሔ ማስቀመጥ ዋነኛ ግብ ነው። ይህ የሚተገበርበት ዋናው መንገድ በተቋሙ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት በዕለት ከዕለት  ሥራዎች ውሰጥ በማስገባት የአመራሩን ብቃት ማሳደግ፣ በእቅዶች ውስጥ የስልጠና ፕሮግራሞችን መንደፍ፣ የተገኙ የሥራ ውጤቶችን መገምገም  እና ቀጣይነት ያለው ውጤት ማስመዝገብ የሚሉ ናቸው። አቅም ግንባታ አንድን ሥራ በተግባር ውስጥ በማስገባት በግለሰብ፣ በቡድን፣ በተቋም እና በአካባቢ ማህብረሰብ፣ በብሄራዊ እንደዚ ሁም በአለም ዓቀፍ ደረጃ በተሻለ ሁኔታ የህብረተሰቡን ጥያቄ  በተከታታይ መልኩ ምላሽ የሚሰጥ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢ... ህገ-መንግሥት አንቀጽ 102 መሠረት ነጻና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኛነት እንዲያካሄድ የተቋቋመ ከማንኛውም ወገንተኛነትና ተፅዕኖ ነጻ የሆነ ተቋም ነው፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ የምርጫ ሥራዎችን በብቃት በማከናወን በርካታ ልምዶችን አካብቷል፡፡
አሁን ያለው የቦርዱ አባላትም ከተሰየመበት ሰኔ 1999 .. ጀምሮ ዘርፉ ብዙ የምርጫ ሥራዎች ለማከናወን ችሏል፡፡ ከተከናወኑት ሥራዎች መካከል የቦርዱ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድን በመፈተሽ የእቅድ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ ከተቀመጡት የእቅድ አቅጣጫዎች ውስጥ በዋነኝነት የአቅም ግንባታ ሥራ አንደ ቁልፍ ጉዳዩ ተወስዶ ነበር፡፡ ቦርዱ ከዚህ ቁልፍ ጉዳዩ በመነሳት ለመጀመሪያ ጊዜ ከጽ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር በመመካከርና በመወያየት ሁለንተናዊ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ  የጽ/ቤቱን መዋቅር በአዲስ መልክ ማዋቀር፣ ሠራተኛውን በመዋቅር ውስጥ ማስገባት፣ የተጓደሉትን መዋቅሮች በሠለጠነ የሰው ኃይል በቅጥር ማሟላት እና በየክልሎቹ የቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎችን ማሟላት ነበሩ፡፡ በዚህ መነሻነት ቦርዱ በተለያዩ ርዕስ ጉዳዮች ዙሪያ የራሱን፣ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎችን እንደዚሁም የባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በሥልጠና እና በልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተልኮውን ለመተግበር የሚችለው ብቁና የሰለጠነ የሰው ኃይል ሲኖረው መሆኑ አያጠያይቅም። ይህንኑ ተግባር ለማስፈፀም 2003 በጀት አመት ቦርዱ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥራዎች መስጠት ችሏል፡፡ ከተሰጡት ሥልጠናዎች መካከል የቦርዱን አቅም ለማጎልበት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የተሰጡ ሥልጠናዎች ሲሆኑ፣ በተለያዩ የምርጫ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በየደረጃው ያሉ የጽ/ቤቱ ኃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ሥልጠናዎች እንደሚከተለው ቀርቧል
1 የሀገር ውስጥ ሥልጠናዎች
1.1 ለባለድርሻ አካላት
የኢትዮዽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተቋቋመበት 1987 .. ጀምሮ በተከታታይ በመላው  ሀገሪቱ በሚገኙ ብሔራዊ ክልሎች የጠቅላላ፣ የአካባቢ፣ የድጋሚ እና የማሟያ ምርጫዎች እንዲሁም ሕዝበ ውሣኔዎችን በህገ መንግሥቱና በምርጫ ህጉ መሠረት ማከናወኑ ይታወቃል፡፡ ቦርዱ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ፣ ፈቃድ የመስጠት፣ በህጉ መሰረት የመከታተል እና የመቆጣጠር ሲሆን ከምርጫ ጋር በተያያዘ ያሉባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት የዕለተ ዕለተ አቅም ግንባታ ሥራዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። እነዚህን ተግባራት በሚያከናውንበት ወቅት  ቦርዱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በምርጫ አፈፃፀም ሂደት ዙሪያ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በተለያዩ ወቅቶች ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ለፖለቲካ ፓርቲዎች 2002 . ጠቅላላ ምርጫ የመንግስት የፍይናንስ ድጋፍ የኦዲት ሪፖርት አቀራረብ አስመልክቶ በጽ/ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች እና በመስኩ ባለሙያዎች በቂ እውቀትና ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪ የፋይናንስ ሪፖርታቸው በወቅቱ ያላቀረቡ ፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ከዋናው ኦዲተር ባለሙያ እንዲመደብ ተደርጎ ስለሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሪፖርት ጉዳይ  በዝርዝር ገለፃ በማድረግ ለወደፊት ሥራዎቻቸውን የሚያግዝ ክህሎት  እንዲያገኙ ተደርጓል። ለፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አቅማቸውን  ለማሳደግ በሁለንተናዊ የአመራር ለውጥ /Transformational Leadership/ ዙሪያ፣ በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ህግ እና አፈፃፀም ላይ የአመራሩን ክህሎት የሚያጎለብቱ ሥልጠናዎች  በዘርፉ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ተሰቷል። ይህም  በምርጫ ሕግና አፈፃፀም ያለውን ክፍተት ከማጥበብ አልፎ የሀገራችን ዴሞክራሲ ሂደት ወደ ተሻለ ደረጃ ያደርሳል።
ስለሆነም ቦርዱ በበጀት አመቱ ለፖለቲካ ድርጅቶች ያቀዳቸው የሥልጠና መስኮች ያሳካ በመሆኑ  በቦርዱ እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካካል ያለው ግንኙነት የተሻለ ደረጃ ላይ የደረሰ እና ለወደፊትም  ከዚህ የበለጠ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ በቦርዱ ዕቅድ ተመላክቷል፡፡
         1.2 ለጽ/ቤቱ ኃላፊዎች እሰራተኞች
በጽህፈት ቤቱ  የተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የተሰጡ ሲሆን ከተሰጡት ሥልጠናዎች መካከል በዋነኛነት ለቦርዱ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ለመምሪያ ኃላፊዎች፣ ለክፍል ኃላፊዎች እና ሠራተኞች እንዲሁም ለክልል ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊዎች በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራሞች፣ በመሠረታዊ የሥራ አመራር ክህሎት፣ በመሠረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንትና DIP የአፈፃፀም ስልቶች፣ በዘመናዊ የቢሮ አያያዝ፣ በመሠረታዊ ኮምፒተር ዕውቀት፣ በድህረ ገጽ አጠቃቀም፣ በሪኮርድና ማህደር አፈፃፀም፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን አጠቃቀምና ጥገና፣ የስልክ ኦፕሬተሮች፣ በጂአይኤስ ዙሪያ፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ፖሊሲዎች፣ በበጀት ዝግጅትና ማኔጅመንት፣ በህትመት ዙሪያ በሚመለከታቸው መስክ በየደረጃቸው ሥልጠናዎች ተሰጥቷል።
2 ውጭ ሀገር ስልጠናዎችና የተገኙ የልምድ ተሞክሮዎች
የኢትዮጵያ  ብሔራዊ  ምርጫ  ቦርድ ከተሰጠው ስልጣንና ተግባር መካካል በየደረጃው  እና  በየጊዜው የሚካሄዱ  ምርጫዎች  ነፃ፣  ፍትሃዊ  በሆነ  መንገድ  የሚካሄዱበትን ሁኔታ  የማመቻቸት  እና የማረጋገጥ  ሥልጣን  አለው።  በዚህ መነሻነት ከውጭ ሀገር  ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በመገናኘት ምርጫን አስመልክቶ የሚገኙ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን በመቅሰም ከአገራችን
ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ሲሰራ ቆይቷል። በ2003 በጀት አመትም የቦርዱ ኃላፊዎች እና የጽ/ቤቱ ዋና ኃላፊ ውጭ ሀገር የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና ልምዶች አግኝቷል።   
ከተሰጡ ዋና ዋና ሥልጠናዎች መካከል
·         በደቡብ አፍሪካ ለምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ እንግሊዝኛ ተናጋሪ ሀገሮች በተዘጋጀው Electoral Management Bodies (EMBs) Workshop on Election and Technology, BRIDGE  capacity building training for Election management bodies in Africa /professional development course /
·         በቤልጅየም exchange seminar on international Election Observation, International IDEA joint training  on effective electoral assistance
·         በሞርሽስ centre for parliamentary studies international Electoral affairs symposium
·         በጋና election observer mission BRIDGE trainings, continental wide meeting of the heads of Electoral management bodies /EMBs/
·         በኬንያ orientation refresher Election observation course
·         በሜክሲኮ International workshop on Electoral administration
·         በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ international foundation for Electoral system/IFES/  
ከዚሁ በተጨማሪ የቦርዱ /ቤት ባለሙያዎች ወደ ወጪ ሀገር በመሄድ በጋና አክራ በአውስትራሊያ መንግስት ስፖንሰርነት  በመራጮች ትምህርት፣ በመራጮች ምዝገባ ዓይነቶችና አስፈላጊነት እንዲሁም ከመራጮች ምዝገባ ጋር ተያያዥነት በላቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ተሰቷል።   
  ከተገኙ ልምዶችም ዋና ዋናዎቹ -
·         በህንድ የምርጫ ኮሚሽን በተደረገለት ግብዣ መሠረት share best electoral practices of Election Management Bodies across the world እና በህንድ ምርጫ ኮሚሽን diamond jubilee celebrations ላይ የሀገራችን የምርጫ ልምድ historical background and current status of Ethiopia election በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጹሁፍ በማቅርብ የኢትዮጵያን ልምድ አካፍለዋል።
·         በአሜሪካ  Election observation mission
·         በደቡብ አፍሪካ  study tour to south Africa to the demarcation, legal and political process     
·         በጀርመን  For aboard-based fact-finding tour and exchange of views on the subject conduct of elections
·         በቦትስዋና  Election observation mission
·         የኡጋንዳ ፕሬዝዳንታዊና የፓርላማ ምርጫን በመታዘብ ተሞክሮ ከማግኘታቸውም በላይ  የሀገራችንን የምርጫ ተሞክሮ ለሌሎቹ ሀገሮች ልምድ አካፍለዋል። በዚህ የልምድ ልውውጥ ላይ ቦርዱ ጥሩ ልምዶችን ቀምሯል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 2003 በጀት አመት በአቅም ግንባታ ዙሪያ አቅዶ የተገባራቸው ሥልጠናዎች የተሻለ የምርጫ ልምዶች እና እውቀቶች ከማገኘቱም በተጨማሪ በአገራችን ወደፊት የሚካሄዱ ምርጫዎች ይበልጥ በማሳካት የዴሞክራሲ ስርዓቱን የላቀ ደረጃ ለማድረስ ከወዲሁ እዲዘጋጅ አቅም ፈጥሮለታል፡፡





No comments: