About Me

My photo
Independence, Neutrality, Rule of the Law, Impartiality and Transparency.

Tuesday, December 13, 2011

ሥርዓተ-ዖታና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ!




ዖታ ወንድና ሴትን ለመለየት አብዛኛውን ጊዜ የምንጠቀምበት ሲሆን፣ሥርዓተ ዖታ (gender) ከዚህ ስያሜ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ተደርጐ ይወሰዳል። ሆኖም የወንድና የሴት ሚናዎች እንደየአካባቢው ባህል ስለሚለያይ ሥርዓተ ዖታ ተለዋዋጭ ጽንሰ ሃሳብ ያለው ነው።
ዖታ ማለት  የሰው ልጆች ሥነ ሕይወታዊ እውነታ ነው። በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለውን የሥነ ሕወይት ተፈጥሯዊ ልዩነት ያመላክታል።  ሰዎች ሴት ወይንም ወንድ ሆነው ይወለዳሉ። ይህ ልዩነት  ተፈጥሯዊ፣ ዓለማቀፋዊ እና ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው። በዚህ የተፈጥሮ ልዩነት መሠረት በሰው ልጆች መካከል አንዳንድ የሚና ልዩነቶች ተከስተዋል። ለምሳሌ፦ ሴት ታረግዛለች፣ ትወልዳለች፣ታጠባለች። ወንዶች እነዚህን ተግባራት ለመፈፀም የሚያስችል የተፈጥሮ ፀጋ አልታደሉም።
ሥርዓተ ዖታ ማለት ደግሞ ሥነ-ተፈጥሯዊ ሳይሆን በማህበረሰብ ውስጥ ያለ የአስተሳሰብ እና የአመለካከት ውጤት ነው። ሥርዓተ ዖታ አዲስ ፍቺ የተሰጠው ጥንታዊ ቃል ነው። በውስጡም በርካታ የተዛመዱ ሃሳቦችን የያዘ ጥምር ቃል ነው። የሥርዓተ ዖታ ጽንሰ ሃሳብ ማወቅ በልማት ሂደት በወንዶችና ሴቶች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለማወቅ ይረዳል። ሥርዓተ ዖታ አንድ ማህበረሰብ በሚኖረው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ አኗኗር  ውስጥ የተፈጠረና የሚፈጠር  እንዲሁም በሴቶች እና በወንዶች መካከል ያሉትን  የሥራ ግንኙነት ሁኔታዎችንና  ሂደቶች የያዘ ጽንሰ ሀሳብ ነው። ሥርዓተ-ዖታ በልማትና በዕድገት ዕቅዶች ውስጥ በስፋት እየተካተተ ቢሆንም በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ግን በአብዛኛው ግንዛቤ አልተቸረውም። በአብዛኛው የአለም ሀገሮች በሥርዓተ ዖታ ዙሪያ የሚነሱት ጥያቄዎች በአመዛኙ ከሴቶች የመብት ጥያቄዎች ጋር ያዥነት ያላቸው በመሆኑ የሥርዓተ ዖታ አሠራርም በአንድ ወገን ለሴቶች ብቻ የቆመ እንደሆነ ተደርጐ ይታሰባል።
በዓለም አቀፍም ሆነ በሃገራችን ስርዓተ ፆታ የልማት እና የዴሞክራሲ ጉዳይ ሆኖ ትኩረት የተሰጠው መሆኑ  ይታወቃል። ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ ለማሻሻልና ለማስተካከል ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥና  በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ መስኮች ተሳታፊነታቸውን እና ተጠቃሚነታቸውን ከመቼውም ጊዜ በላይ በማጠናከር ረገድ ፈር ቀዳጅ የሆኑ እርምጃዎች ተወስዷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሃገራችን ለመተግበር ከተያያዘችው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አኳያ የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት  ለማስቀጠል በቁልፍ ተግባር ታቅዷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲጨምር መመሪያዎችንና ደንቦችን ማውጣቱ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ የገንዘብ ድጎማ ቀመር ለሴት ተወዳዳሪ ዕጩ ላቀረቡ 10 ከመቶ እንዲያገኙ እና በየደረጃው የሚገኙ የምርጫ አስፈፃሚዎች የሴቶች ውክልና እንዲኖር አድርጓል፡፡ አሃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዮት በ1987 . እስከ 2002 . ተመርጠው በህዝብ ተወካዮች እና በክልል ምክር ቤቶች  የገቡ ሴቶች እድገት እያሳየ መምጣቱን ያመለክታል፡፡

.

.
መቀመጫ ያገኙ ሴቶች

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
በክልል ምክር ቤት
በቁጥር
በፐርሰንት(%)
በቁጥር
በፐርሰንት(%)
1
1987
13
2.38
77
5.3
2
1992
42
7.68
244
12.95
3
1997
117
21.4
517
26.43
4
2002
152
27.79
515
27.05

ቦርዱ ሴቶች በመራጭነትና በተመራጭነት ያላቸውን ተሳትፎ የበለጠ እንዲጨምር በ2003 ዓ.ም በጸደቀው የቦርዱ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ የሥርዓተ ዖታ ጉዳይ አንዱ የትኩረት አቅጫ መሆኑን አስምሮበታል። በመሆኑም ለመገናኛ ብዙሃን ሴት ጋዜጠኞች፣ ለህዝብ ተዎካዮች ምክር ቤት እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሴት አባላት ተሳትፏቸው እንዲጎለብት ስልጠና በመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በጽ/ቤቱ 241 አጠቃላይ ሠራተኞች ውስጥ 93 ሴቶች ሲሆኑ፣ በአመራርነት ደረጃም ከቦርዱ አባላት እስከ ታችኛው እርከን ድረስ የሴቶች ተሳትፎ ካለፉት በተሻለ ሁኔታ ጨምሯል። ሴቶች በመራጭነት ያላቸው ተሳትፎ ከፍተኛ ቢሆንም በተመራጭነት ግን ዝቀተኛ ነው። በዚህ ዙሪያ ፖሊቲካ ፓርቲዎች ሴት ዕጩዎችን በማቅረብ በኩል ትኩረት ሰጥተው ሊንቀሰቀሱ ይገባል።
በየደረጃው የሚገኙ የፅሕፈት ቤቱ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሥርዓተ ዖታን  በዕቅዳቸው ውስጥ  አካተው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸውና በፅሕፈት ቤቱ ያሉ ሴቶች በሚያደርጉት የዕለተ ዕለት የስራ እንቅስቃሴ በተለይም ደግሞ በምርጫ አፈፃፀም ጉዳዮች ላይ ክሕሎታቸውንና ዕውቀታቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ በማድረስ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታው የላቀ ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያስቻል ነው። የሴቶች ተሳትፎ በማንኛውም መስክ ይብልጥ ለማጎልበት ሴቶችን ማስተማር፣ የዖታ ልዩነትን ማጥበብ፣ የሥርዓተ ዖታ ግንዛቤ በሁሉም ዘንድ እንዲኖር በማድረግ ሀገራችን የያዘችውን እቅድ ማሰካት ይገባል።
                                                                                         



No comments: